የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት 4ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።
የብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ በጉባዔዉ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በፍጥነት ለማደግ እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት ይኖርብናል ብለዋል።




በክልሉ ህገ_መንግስት በተሰጠው ስልጣን መሰረት በክልሉ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴት እንዲጎለብት ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የህብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥና ተፈጻሚነት እንዲኖረውም ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ መቱ አኩ ተናግረዋል ።
የጋራ እሴቶችን በጋራ ማልማት፣ መንከባከብና መጠቀም ይኖርብናል ሲሉም አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ ተናግረዋል ።
በ2018 የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች በዓል ቀንን በክልሉ ሁሉም አካባቢ የህዝቦችን አንድነትና ትስስርን በማጠናከር እስከ ማጠቃለያው ቀን ድረስ በድምቀት ይከበራል ሲሉም ተናግረዋል ።
በክልሉ ሰላምን በዘላቂነት ለማስቀጠልም የሰላም እሴቶቻችንን በማጠናከር ክልላዊ የመልማት አቅማችንን በጋራ ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ።
የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት 4ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ 3ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ቀርቦ በምክርቤት አባላት አስተያየት በመስጠት ጸድቋል።
በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ መቱ አኩን ጨምሮ ሌሎችየክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የምክርቤት አባላት ተገኝተዋል ።
በታጠቅ አበበ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
