ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ሃሳቦች
# ኢኮኖሚን በተመለከተ ባለፉት ስምንት ወራት በዋና ዋና የኢኮኖሚ አመላካቾች ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል። በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ይህን ስኬት ማጠናከር ከተቻለ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ነጥብ 4 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች። # ግብርናን በተመለከተ በግብርና ምርት የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል። በስንዴ ልማትም በመኸር 4 ነጥብ…
