




የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በሸካ ዞን በኮሙኒኬሸንና ሚዲያ ሥራዎች ዙሪያ ድጋፍ ክትትል ስራዎችን አድርጓል።
የቢሮዉ አመራሮችና ባለሙያዎች በሸካ ዞን የዞን ማዕከል ፣ የአንድራቻ ወረዳ ፣ የየኪ ወረዳና ቴፒ ከተማ አስተዳደር ተግባር አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ምልከታ አድርገዋል።
በድጋፍ ክትትሉ በዕቅድ ዝግጅት፣በሰው ኃይል ስምሪት፣ በኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት፣በሚዲያ ሞኒተሪንግና በህዝብ አስተያየት ጥናት ዕቅድ እንዲሁም የመንግስት መረጃና ዲጂታል ሚዲያ ዘርፎች ተግባራት አፈፃፀሞች ያሉበት ደረጃን በስፋት ተገምግሟል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር መስፍን ወዳጆ እንዳሉት የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በብዛት በመጠቀም የመረጃ ተደራሽነት ችግሮችን ለመቅረፍ መሰራት አለበት ብለዋል።
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎችን ለማሳለጥ በዞኑ የሚደረግ እንቅስቃሴ የሚበረታታ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ዕቅዶችን በአንድ ዕቅድና አንድ ሪፖርት መርህ እስከታችኞቹ መዋቅሮች የማናበብና የመተግበር ጉዳይ ፈጥኖ ወደ ሥራ መገባት እንዳለበት ዶክተር መስፍን አሳስበዋል።
ከህዝብ አስተያየትና ሚዲያ ሞኒተሪንግ አካባቢ የሚስተዋለው ክፍተት ልታረም ይገባል ሲሉም በአፅንኦት አንስተዋል።
የሸካ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አድራሮ በበኩላቸው ተቋሙ በዘርፉ የተሰጠውን ተልዕኮና ተግባራት ለማከናወን እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች በመሆኑ ይህንን ተግባራት በሁሉም መዋቅሮች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የሸካ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምንተስኖት እንዳሻው በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን እያደረገ ያለው ድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በግብረመልሱ ላይ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በወቅቱ እንደተናገሩት የተሰጠውን ግብረ መነሻ በማድረግ የተሻለ የኮሙኒኬሽን መዋቅር ለመፍጠር በትኩረት ይሠራል ብለዋል።
በድጋፍ ክትትል ግብረ መልስ ላይ የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር መስፍን ወዳጆ ፣ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አቶ አበበ ማሞን ጨምሮ የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎችና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።
