“ጉልፋ”-የናይዎች ጥበብ

Spread the love

ናይዎች በክልላችን ከሚገኙ የውብ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ከሆኑ ህዝቦች መካከል ይጠቀሳሉ።

ባህላቸው ውበታቸው፣ ህይወታቸውም ነው።ናይዎች በፍቅር ሲጠጓቸው ያላቸውን ሁሉ ይሰጣሉ።የማስመሰል ዝምድናን አያውቁም።

ናይዎች ደስታቸውን በተለያየ መንገድ ይገልፃሉ። በደስታ ጊዜ ስሜታቸውን የሚገልፁበት መሳሪያ የትንፋሽ መሳሪያ “ጉልፋ” ይባላል። “ጉልፋ” ከቀርከሀ የሚሰራ ነው።

በአንደ ጊዜ የትንፋሽ ድምፅ የሚያወጣ “ጉልፋ” በቁጥር አምስት ሲሆን አንዱ ቢጎል መሳሪያዉ መልእክት ያለዉን ድምጽ እንደማያሰማ የማህበረሰቡ አባላት ያስረዳሉ። አምስቱ መሳሪያዎች ተባብረው “ጉልፋ”ን ይፈጥራሉ።

ይህም የሰው ልጅ አምስቱ ጣቶች ሲተባበሩ የሚፈጥሩትን አቅም የሚገልፅ ምሳሌ ተደርጎ ይታመናል። የአንድነት ምልክት እንደሆነም ማሳያ ነው።

ናይዎች በየአመቱ የሚከበረው የወንድማቸው የካፈቾዎችን ማሽቃሮ በዓል አብረው በማክበር ያደምቃሉ።

ዘንድሮም ከቀበሌያው እስከ ቦንጋ ሻንባቶ የተከበረውን ማሽቃሮን በ“ጉልፋ” አድምቀውታል፡፡

አብሮነትን በሚጎላው በማሽቃሮ አደባባይ ተገኝተው በ“ጉልፋ” ሲያደምቁ በባህላዊ አልባሳታቸው ያምራሉ፡፡

ባህላዊ እሴቶች ለቀጣዩ ትዉልድ እንዲሸጋገሩ የድርሻ እንደሚወጡም በካፈቾ ብሄር ማሽቃሬ ባሮ ላይ የታደሙ ናይ ብሄረሰብ አባላት ተናገረዋል።

እጅግ ውብ የሆኑ ባህላዊ እሴቶች በጎባ ወረዳ እንደሚገኙ ያስረዱት የወረዳዉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጋሻዉ ኬቶ የማህበረሰቡን እሴቶች ለማልማትና ወደ ቀጣይ ትዉልድ ለማሸጋገር ዘርፈ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ገለፀዋል።

የናይ ብሄረሰብ የበርካታ የቱባ ባህሎች ባለቤት መሆኑን አንሰተዋል ሲል ካፋ ቴቪ ዘግቧል።

“ጉልፋን” ጨምሮ የተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶችን ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *