







በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ና የሱፐርቪዥኑ መሪ የሆኑት በአቶ ነጋ አበራ የተመራው ልዕካን ቡድኑ በዞኑ ፓርቲና መንግሥት የተከናወኑ ተግባራትን፣ የታዩ ጥንካሬዎችን እና ክፍተቶችን እንዲሁም የተገኙ ምርጥ ልምዶችን በመለየት በቀጣይ ጊዜያት ይበልጥ እንዲከናወኑ የሚያስችሉ ተግባራት አፈፃፀም ገምግሟሉ፡፡
በድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ሂዴቱ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ዓመታዊ ዕቅዱ በተቀመጠው ግብና አቅጣጫ ስለመፈፀሙ፣ ለፓርቲው እሴት ሊጨምር በሚችል መልኩ ምክረ-ሀሳብ እያቀረበ ለፓርቲው ሁለንተናዊ ለውጥ እያደረገ ያለዉ አስተዋጽኦ በሱፐርቪዥን ቡድኑ በጥልቀት ተገምግሟል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ የፓርቲና መንግስት ሥራዎች ሱፐርቪዥን ቡድን በዳውሮ ዞን የሚያካሂደው የድጋፍና ክትትል ሥራ በዞኑ ላሉት ሁሉም መዋቅሮችና አደረጃጀቶች ዘላቂ አቅም እንደሆነም ተናግረዋል።
በድጋፋዊ ክትትል ሥራ መነሻ በየደረጃው መሰረታዊ ለውጥ በሁሉም መስክ እየተሰራ ያለው ሥራ በመንግሥት እና በፓርቲ የተጀመሩ ተግባራት የተሻሉ ጅምር ሥራዎች በተላይ ፓርቲው ሰው ተኮር በመሆኑ በአመራርና በአባላት እንዲሁም ሁሉንም ማህበረሰብ አካላት ተሳትፎ ድምር ውጤት በተጨባጭ በተገኙ ድሎችና ሌማት ትሩፋቶች ደስተኛ መሆናቸውን አቶ ነጋ ገልጸዋል።
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበዬሁ በበኩላቸው ድጋፋዊ ክትትልና ሱፐርቪዥን ሥራ ለጠንካራ ፓርቲ እና ለጠንካራ መንግስት መሠረት እንደመሆኑ መጠን ፓርቲዉ በሚያደርገዉ እንቅስቃሴ የቡድኑ ድጋፍ ወሳኝ ነዉ ብለዋል።
በቅርቡ እንደ ዞን ያሉን አደረጃጀቶችን እንደገና በሰራነው ማግስት እየተደረገ ያለው ድጋፍና ሱፐርቪዥን ቀጣይ እስከ ታችኛው ያሉ የፓርቲው መዋቅሮች ያሉበትን ቁመና ለማየት ዕድል ይሰጣል ብለዋል።
ሱፐርቪዥኑ በአስተሳሰብና አመለካከት የታነጻ አመራርና አባል ለማፍራት፣ ፓርቲን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት እንዲሁም ጠንካራ አባልና አደራጃጀትን ለመፍጠር እንደሚያግዛቸው የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ ገልጸዋል።
በመድረኩ ለቀጣይ ትኩረቶ ማድረግ የሚፈልጉ ነጥቦች የሥራዎች ጥራትና ጊዜ አጠቃቀም፤ብዙኃን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያ፤ ከህዝብ ስብጥር፣ ፊላጎትና ልማት ጥያቄ አንፃር ፖለቲካል እይታ ጠንካራ ዕቅድ በማቀድ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።
የአመራር እና የአባላት ቅንጅታዊ ሥራ፤ የፓርቲና መንግስት የመሪነት ሚና ከመጫወት አንፃር፤ የፓርቲ አደረጃጀቶችን በአሠራር መመሪያ ማጠናቀርና ውጤታማ ማድረግ፤ የአስተባባሪ ኮሚቴ ሥራዎችን ማጠናከር፤ የፓርቲና ፖለቲካ ኮሚቴ ሥራዎችን መምራት፤ ጠንካራ መሠረታዊ ድርጅት ከዓላማው አንፃር በአሠራር ማደራጀት፣መምራትና መደበኛ ኮንፈራንስ በወቅቱ ማካሄድ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ውጤታማ ህዋስ መፍጠር፤ የፓርቲ አባላት ማጥራትና ለይቶ መደገፍ፤ ጠንካራ የአመራር ሥርዓት መፍጠር ፤አጀንዳዎች በዕውቀትና በክህሎት አደራጅቶ መምራት፤ጥልቀት ያለውን የፖለቲካ አዝማሚያ ግምገማ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተገምግሟል።
በመጨረሻም በግልና በቡድን ጠንካራ ሚዲያ መትከል ፣ ወቅታዊ በሽታ የመከላከልና ሁሉንም ንቅናቄ አጀንዳዎችን በአግባቡ መምራት እንደሚያስፈልግ ተገምግሞ ግብረ መልስ ተሰጥቶ ሱፐርቪዥን መድረኩ ተጠናቋል።
