የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና አለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ባለፉት አራት ተከታታይ ቀናት በጅማ ከተማ ያዘጋጀው የ3ኛ ዙር የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል።

Spread the love

በስልጠናው የማጠቃለያ መድረክ በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ መመሪያ የሰጡት የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የብሔራዊነትን ትርክት አገራዊ አንድነትና ሕብረ ብሔራዊነትን በማስታረቅ ቅቡልነት ያለው አገረ መንግስት ግንባታ መፋጠን ወሳኝ አምድ በመሆኑ የሚዲያ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ በትኩረት መስራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

አሁን ባለንበት የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ የትርክት የበላይነት ለመውሰድ በፉክክር ሜዳ አሸናፊ ሆኖ መገኘት ግብን ታሳቢ ያደረገ የተግባቦት ስልትን መከተል እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ የውስጥ አቅማችንን በብቃትና በጥራት ከመጠቀም በተጨማሪ አድማስ ተሻጋሪ ሆኖ በማሰብ የጎደንን መሙላት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ንቅናቄ በመፍጠር የብሔራዊ ትርክትን በዕለት ተዕለት የፖለቲካ ህይወት ውስጥ ተናቦና አስማምቶ መጓዝ ከስልጠናው መድረኩ የሚጠበቅ ውጤት ነው፡፡

የማኅበራዊ ሚዲያውን አልጎሪዝም በውል በመረዳት የመልዕክት ቀረጻና ተደራሽነት የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ በሃላፊነት ማስቀጠል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

ባለፉት አራት ቀናት የተሰጡ ስልጠዎችን እንደመነሻ በመውሰድ ተጨማሪ አቅም በማዳበር መዋቅራዊ ቅርጽ ማስያዝ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

#Prosperity

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *