በሸካ ዞን የጥምቀት በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው
የጥምቀት በዓል በሸካ ዞን በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ በቅዳሴ፣ በፀሎት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና እና በሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። ትላንት ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ባደሩበት የባህረ ጥምቀት ሥፍራው ከሌሊቱ ጀምሮ ሥርዓተ ቅዳሴና ልዩ ልዩ ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከናወኑ ያደረ ሲሆን በጠዋቱ ክፍለጊዜም የጥምቀት ስነስርዓት በካህናቱ አማካይነት ተከናውኗል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች…
