በቤንች ሸኮ ዞን የ2017 የግብርና የበልግ ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ

Spread the love

በመድረኩ ላይ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንደገለፁት ዞኑ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ ለይቶ በቅንጅት በመምራት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከምንጊዜ በላይ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

ፓርቲያችን ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በ24/7 መሠረት ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም ለምርትና ምርታማነት በቅንጅት መስራት ከሁሉም እንደሚጨበቅ አሳስበዋል።

በዞኑ በአንድ አንድ የግብርና ስራዎች ላይ የተመዘገበውን የተሻለ ውጤት ባልተሳኩ ተግባራት ላይ መድገም እንደሚያስፈልግ አስተዳዳሪው አሳስበዋል።

በቅድመ ዝግጅቱ ፈፃሚን የማዘጋጀት ተግባር ለማሳካት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በመያዝ ወደ ተግባሩ መግባት ይገባል ብለዋል።

በዞኑ በግብርና ዘርፍ በየወቅቱ እያሻሻሉ በቅንጅት መምራት የአፈር ማዳበሪያ ገንዘብ ያለውን የተጣራ መረጃ በመያዝ ግልጽ የሆነ ስርዓት ማስያዝ ሊኖር ይገባል ብለዋል።

የአፈር ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ በወቅቱ በማቅረብ ለምርታማነቱ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሌማት ትሩፋት ገበያ በማረጋጋት ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በመንደር የባለሙያ እገዛ እያገኙ መስራት እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።

በዞኑ ያሉ ኢንቨስትመንቶች በሰብል እርሻ በቴክኖሎጂ በመጠቀም ለአርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል ።

የቤንች ሸኮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን በበኩላቸው በበልግ ሥራ ባለሙያዎች ለአርሶ አደሩ ቴክኒካል ድጋፍ በመስጠትና አመራሩ የራሱን ድርሻ መወጣት ይገባል ብለዋል።

የግብርና ስራ በአንድ ሴክተር አመራሮች እና ባለሙያዎች ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ ሁሉም አመራር በቅንጅትና በቁርጠኝነት መደገፍ እንዳለበት ተናግረዋል።

ለተግባራዊነቱ ፓርቲው በትኩረት እንደሚከታተል የገለጹት አቶ ደግፌ እስከታችኛው መዋቅሮች ድረስ አሰራር ተዘርግቶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በዞኑ በዋና ዋና እና ሆሊቲካልቸር ሰብሎች በ2017 በልግ 111ሺህ 237 ሄክታር በዘር በመሸፈን ከ8 ሚሊዮን 918 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለማገኘት ዕቅድ መያዙ ተጠቆመ።

የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ የ2017 የበልግ ዕቅድን ሲያቀርቡ እንደገለፁት በአዝርዕት ሰብል 78 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት 3 ሚሊዮን 918 ሺህ 255 ኩንታል ለማልማት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በሚሰራው ስራ በተለይ የበቆሎ ማሳ 70 ከመቶው

የተሟላ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም መታቀዱንም ጠቁመዋል።

በበልግ ከሚለማው 25 ከመቶው በኩታ ገጠም እርሻ የሚለማ መሆን እዳለበት ተናግረዋል።

የአፈር ማዳበሪያን በሚገባ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን እንዲጨምር መሰራት አለበት ብለዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ምርታማነቱ የቀነሰ ወይም ምርት የማይሰጥ 444 ሄክታር የቡና ማሳን የማደስና ነቅሎ በአዲስ ተከላ የመተካት ስራ በቀጣይ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በሌማት ትሩፋት የማር ፣ የወተት ፣ የዶሮ እርባታ በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችንም በዝርዝር አቶ መስፍን ጉብላ አመላክተዋል ።

የበልጉ ሥራ የማስፈፀሚያ መርሃ ግብር ለተሳታፊዎች ቀርቧል።

የግብርና ሥራ ውጤታማ ሲሆን በርካታ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚፈታ በመሆኑ ርብርብ ማድረግ ይገባናል ሲሉ ተወያዮቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *