ለቡና ምርት፣ምርታማነትና ጥራት መረጋገጥ ከቡና ዘር ዝግጅት ጀምሮ በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ

Spread the love

ለቡና ምርት፣ምርታማነትና ጥራት መረጋገጥ ከቡና ዘር ዝግጅት ጀምሮ በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ የክልሉ ቡና፣ሻይና፣ቅመማቅመም ባለስልጣን አመላከተ

የክልሉ ቡና፣ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን በቡና ዘር አዘገጃጀት ላይ ለዞን፣ወረዳ፣ቀበሌ ባለሙያዎች እና ለቡና ዘር አዘጋጅ አርሶ አደሮች የተግባር ተኮር የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ነዉ።

ስልጠናው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ቡና፣ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ከክልሉ ‎ግብርና ቢሮ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በተገኘው በጀት ድጋፍ ነው እየተሰጠ የሚገኘው።

በስልጠናዉ ማስጀመሪያ በክልሉ ቡና፣ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ፣ ለቡና ምርት፣ምርታማነትና ጥራት መረጋገጥ ከቡና ዘር ዝግጅት ጀምሮ እስከ ምርት ሂደት ድረስ በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ለቡና ምርት፣ምርታማነት እና ጥረትን መረጋገጥ ጤናማ የቡና ችግኝ እና ምርታማ ዛፍ እንዲኖር መነሻዉ የቡና ዘር ምርጫ ነው ያሉት አቶ አስራት፣የዘር ምርጫ አቅጣጫ እንዳይስት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በዕውቀት መምራት ይገባልም ብለዋል።

በክልሉ የቡና ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ቢሆኑም ምርታማነት በአንድ አመት ከፍ በሌላኛው ዝቅ የሚልበት ተፈጥሯዊ እና ሰዉ ሰራሽ ተግዳሮት እያጋጠመ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ በ2018 በጀት ምርት ዘመን በምርት ትመና ላይም በልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚሻም አሳስበዋል።

ቡና ሰብል ብቻ ሳይሆን ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኩራት፣ቅርስ፣ታርክ፣ባህል ከመሆን ባሻገር የኢኮኖሚ ዋልታ እንደሆነም የተናገሩት ደግሞ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ ኮጃአብ ናቸዉ።

በክልሉ የቡና ምርታማነት ለመጨመር ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ከዚህም መካከል የተሻሻለ የቡና ዘር ለቡና አርሶአደሮች ማቅረብ፣ያረጁ ቡናዎችን ማደስ፣የቡና ማሳ መንከባከብ ሥራዎች ተጠቃሾች መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ስልጠናዉ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቡና ዘር ጽንስ ሀሳብ፣የቡና ዘር አዘገጃጀት፣በቡና ዘር ጥራት ቁጥጥር እና በቡና ምርት ትመና ላይ የተጋጀ ስልጠና እንደሚሰጥ ከወጣው መርሐግብር ለማረጋገጥ ተችሏል።

በፍቅር ከበደ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *