በውጭ ሀገራት በሥራ ስምሪት

Spread the love

በውጭ ሀገራት በሥራ ስምሪት ለሚገኙና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚቆጥቡ ዜጎች ተጨማሪ ፋይናንስ መቅረቡ ለበለጠ ትጋትና ውጤት የሚያነሳሳ ነው ፦ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

በውጭ ሀገራት በሥራ ስምሪት ለሚገኙና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚቆጥቡ ዜጎች ተጨማሪ ፋይናንስ መቅረቡ ለበለጠ ትጋትና ውጤት እንደሚያነሳሳ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሥራ ዕድል ፈጠራን የማስፋት አካል የሆነ የፋይናንስ አቅርቦትና አካታችነት የትብብር ስምምነት አድርጓል።

ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በሥራ ዕድል ፈጠራና በክህሎት ልማት መስክ ተጨባጭ ስኬት እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል።

በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት የሚላኩ ዜጎችም የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ጭምር ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በውጭ ሀገራት የሥራ ቆይታቸው ያፈሩትን ጥሪት ራሳቸውንና ሀገራቸውን መጥቀም በሚያስችል መልኩ እንዲያውሉት ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናንስ አቅርቦት ሥርዓት በውጭ ሀገራት የቆዩ ዜጎች ተጨማሪ የገንዘብ አቅም እንዲያገኙ በማድረግ ለበለጠ ትጋትና ውጤት የሚያነሳሳ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ፤ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንትና መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍም የፋይናንስ አቅርቦትን በማመቻቸት የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ሙያተኞች ሃሳባቸውን ተግባር ላይ የሚያውሉበትን ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር የገባው የፋይናንስ አቅርቦትና አካታችነት የትብብር ስምምነትም የሥራ ዕድል ፈጠራን የማስፋት አካል እንደሆነ አስረድተዋል።

በተለያዩ ሀገራት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ስምሪት ተሰጥቷቸው ገንዘባቸውን በባንኩ ሂሳብ ለሚቆጥቡ ዜጎችም ተጨማሪ ፋይናንስ እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል።

የባንኩ ተጨማሪ የገንዘብ አቅርቦትም በሥራ ስምሪት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ለቤትና መኪና መግዣ እንዲሁም ለሥራ ፈጠራ እንዲያውሉት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል።

የተቋማቱ የትብብር ስምምነት ወጣቶችንና በውጭ ሀገራት በሥራ ስምሪት የሚገኙ ዜጎችን የፋይናንስ አቅርቦት ፍላጎት በመደገፍ የሥራ ዕድል የመፍጠር አስተማማኝነትን በሚያልቅ ማዕቀፍ የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *