ለውጭ ገበያ ከቀረበ ዕጣን

Spread the love

ለውጭ ገበያ ከቀረበ ዕጣን ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረበ የዕጣን ምርት ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮሙኒኬሽንና ማኅበራዊ ኃላፊነት ሥራ አመራር ሥራ አስኪያጅ ጋሻው አይችሉህም 2 ሺህ 505 ኩንታል ዕጣን ወደ ቻይና፣ ዱባይ፣ ግሪክ፣ ቱኒዝያና ቱርክ በመላክ ከ1 ሚሊየን 641 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

260 ኩንታል ዕጣን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ከ7 ሚሊየን 710 ሺህ ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸው÷ በዚህም የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለው አንስተዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከሚሰበስበው የዕጣን ምርት ከ90 በመቶ በላይ ያህሉን ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ጠቁመዋል።

በዘርፉ የሚስተዋል ሕገወጥ ንግድ እና ሌሎች ተግዳሮቶች ሀገሪቱ ከተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን ሽያጭ በሚፈለገው ልክ ተጠቃሚ እንዳትሆን ማድረጉን አመላክተዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት 2 ሺህ 510 ኩንታል የዕጣን ምርት ወደ ውጭ በመላክ ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ ታቅዷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 

👇
📌

በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌

በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌

በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌

በትዊተር twitter.com/sweprs

📌

በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌

በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌

በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌

በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌

በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *