







በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 2ኛዉ ዙር ሀገር ዓቀፍ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ
ስልጠናዉ ”በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል ሃሳብ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዚህም የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም የሚገነቡ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚቀርቡበት መድረክ ነዉ።
ስልጠናውን ያስጀመሩት በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ብልጽግና ፓርቲ ሰፊ ሃሳብ ያለው፤ በሃሳብ የሚሠራ እና በሃሳብ የሚመራ ትልቅ ፓርቲ እንደሆነም ገልጸዋል።
ስልጠናው የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም ከመገንባት ባሻገር የመፈጸም እና የማስፈጸም ብቃት ያላቸው አመራሮችን ለማፍራት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
በመደመር መንግስት እይታ የገጠር የመዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ፣የኢንዱስትሪ ዘርፍ ፣የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ በሚሉ አጀንዳዎች እንደሚያተኩርም አንስተዋል።
ፓርቲው የጀመራቸው የብልጽግና ጉዞዎችን ለማስቀጠል ተግባራትን በመፍጠር፣ በመፈጠን እና ሥራዎችን በጥራት ማከናወን እንደሚገባም አመላክተዋል።
በለውጥ ሂደት ውስጥ ያሉ ውጤቶችን በመገንዘብ የሚገጥሙ ፈተናዎችንም በጋራ ለመፍታት የአመራሮችን አቅም መገንባት ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል።
ስልጠናው የአመራሩን የተግባር አንድነት የሚያሳድግ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት የሚያረጋግጥ እንዲሁም የተግባራት ውጤታማነትን እንደሚያሳድግ ነው አቶ ፍቅሬ አማን የገለጹት።
ዛሬ በተጀመረዉ ስልጠና ከ680 በላይ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በፍቅር ከበደ
