ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤን ማዘጋጀቷ ለዘርፉ የሰጠችውን ትኩረት ያሳያል፦ የዓለም የጤና ድርጅት

Spread the love

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤን በአድዋ ድል መታሲያ እያስተናገደች ትገኛለች።

የዓለም የጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ኦውን ካሉዋ በጉባኤው፥ የጤናው ዘርፍ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን እንዲያቅፍ እና በአባል ሀገራት የጤና ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ ድጋፍ በማደረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በትብብር ከተሠራ ምንም የማይቻል ነገር የለም ያሉት ተወካዩ፤ በየጊዜው የሚያጋጥም ወረርሽ እና ተላላፊ በሽታንም በተመሳሳይ በጋራ መከላከል እንደሚቻል አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤን ማዘጋጀቷ ለዘርፉ የሰጠችውን ትኩረት ያሳያል ብለዋል።

ሀገሪቱ የጤና ሥርዓቷን ይበልጥ ለማሻሻል በምታደርገው ጥረት የዓለም የጤና ድርጅት እገዛ እንደሚያደርግም ገልፀዋል።

ከ800 በላይ ተሳታፊዎች በታደሙበት ጉባኤ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችን ማዘመን እና ማስፋፋትን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ችግር ፈቺ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *