የወረዳ የማህበረሰብ ወኪሎች በአጀንዳዎቻቸው ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

Spread the love

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ የማህበረሰብ ወኪሎች ከትላንት ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም ከሰዓት ጀምረው ከወከሉት ማህበረሰብ ይዘዋቸው የመጡ አጀንዳዎችን በውይይት በማደራጀት ላይ ናቸው፡፡

በዚህ የምክክር መድረክ ከ57 የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ 1003 የሚሆኑ የዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

እነዚህ የወረዳ የማህረሰብ ክፍል ወኪሎች ምክክራቸውን እስከ ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የምክክር መድረክ ትላንት ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም በቦንጋ ከተማ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *