ሀገራዊ ምክክሩ በሀገራችን እስከአሁን የነበሩ ችግሮች በንግግርና በምክክር ለመፍታትእጅግ ጠቃሚ ነው፦ አስተያየት ሰጪ መምህራንና የመንግሥት ሠራተኞች

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትናንት ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም በጀመረው አጀንዳ ማሰባሰቢያና ተወካይ መረጣ መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ በክልሉ ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ከትላንት ከሰዓት ጀምረው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ሲያደራጁ ቆይተዋል፡፡

በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙ መምህራንና መንግሥት ሠራተኞች የምክክር ሂደቱ የሀሳብ የበላይነትንና ነፃነትን ለማረጋገጥ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

ከተሳተፉት መምህራን መካከልም መ/ር ንጉሴ ዓለሙ ከካፋ ዞን እና መ/ር አለማየሁ ምትኩ ከኮንታ ዞን የምክክሩ ተሳታፊ ናቸው።

በውይይቱ በርካታ ሀገራዊና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ አጀንዳዎች እያደራጁ ስለመሆናቸው ገልጸው ፣ አጀንዳዎቹ ተቀባይነት ኖሮአቸው ወደ ተግባር ከተቀየሩ ኢትዮጵያን አንድ ሚያደርጉና ወደ ሚፈለገው ብልጽግና ማማ ላይ እንዲትወጣ የሚያስችል ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

መ/ርት አበራሽ አቡ ከምዕራብ ኦሞ ዞን የተሳተፈች ሲትሆን ምክክሩ ምንም አይነት የሀሳብ የበላይነት እና ነፃነት ሳይገደብ እያንዳንዱ የማህበራዊ መሠረት ተወካይ ለአጀንዳ የሚሆኑ ሀሳቡን እያቀረበ መሆኑንና የሀሳብ ግጭቶችንም እያስማመንና ወደሚያግባባ ሀሳብ እያመጡ የምክክር ሂደቱን እየተካሄደ መሆኑን አውስታለች።

ሲስተር ሙሉአለም ተፈሪ ከዳውሮ ዞን መንግሥት ሠራተኞች ተወካይ ሲትሆን፣ በምክክር ሂደቱ የሀሳብ ነጻነትን መሠረት በማድረግ እያቀረቡ ስለመሆናቸውና ምክክሩ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ለውጥ አምጪ መሆኑን ጠቁማለች፣ በምክክሩ መነሻ የተነሳ እያንዳንዱ አጀንዳ በትክክል ተደራጅቶ በተገቢው ከተሰራና ለችግሮቹ በጋራ ምላሽ አምጭ ምክክሮች ቀጣይነት ባለው መልኩ ከተደረገ እንደሀገር ውጤታማ መሆን ይቻላል ነው ያለችው፡፡

አቶ አለማየሁ ዳንኤል ከቤንች ሸኮ ዞን መንግሥት ሠራተኞች ተወካይ ሲሆን፣ በምክክሩ ሀገሪቱን ሊገነባ የሚችሉ ሀሳቦችን ተሳታፊዎች በነፃነት እያነሱና በጋራ በመመካከር አጀንዳዎቻችንን እያጣጠናከርን ነው ያሉት፡፡

እንደሀገር የጋራ ችግሮቻችን ምን እንደሆኑ በመለየት ውጤት ለማምጣት የመንግሥት እና የህብረተሰብ ድርሻ ምን እንደሆነ የዳሰሳ የምክክር መድረክ መሆኑንና በቀጣይ ቀጣይነት ሊኖር ይገባልም ብለዋል።

ከሸካ ዞን የኪ ወረዳ የተሳተፈችው የመንግሥት ሠራተኞች ተወካይ ወ/ሮ አብነት አድራሮ በበኩሏ ከቤተሰብ ጀምሮ በመመካከር እና በመደማመጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልጻ ሀገራዊ ምክክሩ በሀገራችን እስከአሁን የነበሩ ችግሮች በንግግርና በምክክር ለመፍታት መንግሥት የጀመረው ጥሩ ጅምር ነው በማለት አስተያየቷን ሰጥታለች።

በአሁኑ ሰዓት ትላንት የጀመረውን የምክክሩ ሂደት የቀጠለ ሲሆን ተሳታፊዎች ለሀራዊ አጀንዳ ይሆናል ያሏቸውን ሀሳቦቻቸውን በቡድን በቡድን ሆነው ወደ አንድ በመሰብሰብና በማጠቃለልም ላይ ይገኛሉ፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *