መጋቢት 24 የኢትዮጵያን የዘመናት ስብራት ለመጠገን ቃልኪዳን የተገባበት ነው:-አቶ ዳዊት ገበየሁ

Spread the love

የሀገራዊ ለውጡን 8ኛ አመት አስመልክቶ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በሰልፋ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ፤ሰልፉ በቃላት ብቻ የማይገለፀውንና በተግባር የታየውን የለውጥ ጉዙ እውቅና ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ የዘመናት ስብራት እንዲጠገን ቃል የተገባበትና ትንሳኤዋን የወሰነ ዕለት መሆኑን ጠቁመዋል።

በሀገራችን በፖለቲካ፣በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዘርፍም ሰው ተኮርና የሀገሪቱን ገፅታ የለወጡ በርካታ ተግባራት የለውጡ ፍሬዎች ናቸው ብለዋል አቶ ዳዊት።

በመጨረሻም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ሰልፉ በፈረስ ጉግስ፣በፖሊስ ትርዒት፣በኪነት ባንዶች ባህላዊ ጭፈራና በተለያዩ ኩነቶች በድምቀት ተካሂዶ፤ በመጨረሻም የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በጋራ በመዘመር ተጠናቋል።

የክልል ማዕከል ታርጫ ክላስተር አመራሮች፣የዳውሮ ዞን፣የታርጫ ከተማ አስተዳደርና የታርጫ ዙሪያ ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የዞኑ ህዝቦች በነቂስ በመውጣት በሰልፉ ተሳትፈዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *