




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛዉ ዙር የግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል።
በመረሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንደገለፁት፤ ሀገራችን በማደግና በመለወጥ ካደጉት ሀገራት ተርታ እንዲትሰለፍ በግል ዘርፍ የሚሳተፉ አካላት ሚናቸው የላቀ ነዉ።
በክልሉ በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ እና በሌሎች ዘርፎች የሚሳተፉ የግል ዘርፎችን የጋራ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅተው የማበረታታት እና የመደገፍና ሥራ ተጠናከሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በ3ኛዉ ዙር የክልሉ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች በመሆን እውቅና እና ሽልማት የተበረከተላቸው ታማኝ ግብር ከፋዮች ብቻ ሳይሆኑ አምራች፣ አቅራቢ እና በከፍተኛ ሁኔታ ምርት በማምረት ገበያ የሚያረጋጉ እንደሆናቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።
ክልሉ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ ፣ በማዕድን በቱሪዝም ዘርፍ በመሰማራት ማልማት ለሚፈልጉ አካላት ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉም ያብራሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ።
በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው ገቢ አሰባሰቡ እንዲጠናከር ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ምቹ ስነ ምህዳር የመፍጠሩ ሥራ በትኩረት ይከናወናልም ብለዋል።
ክልላዊ የገቢ አቅም እንዲያድግም ግብር ከፋዮች ኃላፊነታቸው በብቃት ሊወጡ እንደሚገቡም አሳስበዋል።
ለክልሉ ልማት ግብር በወቅቱና በታማኝነት የሚከፍሉ አስር ታማኝ ግብር ከፋዮች በመንግስት፣ ግል ተቋማትና በማንኛውም በሚንቀሳቀሱበት ቦታዎች ቅድሚያ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በህግ የተፈቀደ አረንጓዴ መታወቂያ እንደተዘጋጀላቸዉ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ባለሃብቶች በቤት ልማት አቅርቦት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ መንግስት አስፈላጊዉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በክልሉ የሚሰበሰበው ገቢ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ለማስቻል ቢሮዉ የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶችን ዘርግተው እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል።
ግብራቸውን በታማኝነት የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ቁጥራቸው ከፍ እንዲል በየደረጃቸው ትኩረት ተሰጥተው እንደሚሰራም ኃላፊዋ አመላክቷል።
ክልላዊ የገቢ አቅሞችን በጥናት በመለየት በሂደቱም የገቢ አፈጻጸምን ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ነው ወ/ሮ ህይወት አሰግድ ያብራሩት።
በ3ኛዉ ዙር ግንባ ቀደም ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብሩ ለታክስ ህግ ተገዥ ለሆኑ 79 ደረጃ ”ሀ”፣ ”ለ” እና ”ሐ” ግብር ካፋዮች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በ2017 ግብር ዘመን የግብር ዕቅዳቸውን በላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞን፣ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ገቢ መዋቅሮች እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
በአጠቃላይ አፈጻጸም ካፋ ዞን፣ቤንች ሸኮ ዞንና ሸካ ዞን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ያለዉን ደረጃ በመያዝ ተሸላሚ ሆነዋል።
የዓመቱን ዕቅድ በ10 ወራት በማጠናቀቅ ኮንታ ዞን፣ ቦንጋ ከተማ፣ሸኮ ከተማ፣ቤሮ ወረዳና ቢጣ ወረዳ ተሸላሚ ሁነዋል።
የወንዶ ኩባንያ አክሲዮን ማህበርም ለክልሉ ገቢዎች ልማት ላበረከተዉ አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ ነዉ።
በፍቅር ከበደ
