




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት 2017 በጀት ዓመት የ3ኛዉ ዙር የግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ባዘጋጀው በዚሁ መረሐ ግብር በ2017 በጀት ዓመት ግብር ዘመን በክልሉ ለታክስ/ግብር ህግ ተገዥ ለሆኑ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል።
ከግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች በተጨማሪም በግብር ዘመኑ የግብር ዕቅዳቸውን በላቀ አፈፃፀም ላከናወኑ መዋቅሮችም እውቅና እና ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
በመርሐ ግብሩ የክልሉ አስተባባሪ አካላትን ጨምሮ የክልል፣ ዞን ፣ወረዳና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በፍቅር ከበደ
