







ምርጫው ፍትሀዊ ፣ ሰላማዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ፓርቲዎች በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጸሐፊና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ ) አመራር አቶ ሰለሞን መኮንን እንደተናገሩት ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫው ፍትሀዊ ፣ ሰለማዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የጋራ ምክር ቤቱ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
መንግስት የፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ምህዳርና ዲሞክራሲን በመጠቀም ፓርቲዎች ሀሳባቸውን መሸጥና ሰላማዊ የምርጫ ሂደት እንዲኖር ማድረግ ይገባል ብለዋል። የምርጫ ህጉን ማክበር ፣ ህገመንግስታዊ ስርዓቱን አክብሮና አስከብሮ መስራት ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንደተናገሩት አንድ የጋራ ሀገር ነው ያለን ፤ ለጋራ ሀገራችን በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ሰላም ፣ ልማት ፣ ዕድገትና ዲሞክራሲ የሁላችንም የጋራ አጀንዳ ነው ያሉት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች መገፋፋት ፣ ማግለልና ስም መጠፋፋትን በመተው ሀሳብ ሽጠን በህዝብ መመረጥ ላይ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
በሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ የህግ የበላይነትን ማክበር ፣ በተዘጋጀው ምቹ የምርጫ ስነ ምህዳር በመሳተፍ ረገድ በጋራ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ሀገርን ለማጽናትና የሀገረ መንግስት ግንባታውን እውን ለማድረግ ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት ወሳኝ ነው ብለዋል። የጋራ ምክር ቤቱም እንደዚህ አይነት ተከታታይ የስልጠናና የምክክር መድረኮችን ሊያዘጋጅ እንደሚገባም ገልጸዋል ሲል የቤንች ሸኮ ቴቪ ዘግቧል።
