



የቢሮ ሀላፊ የሆኑት ኢንጂነር በየነ በላቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ በመሆኑ የተለያዩ አጋር አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።
በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃና ሌሎች መሰረት ልማት አነስተኛ እንደነበረ ነው ኢንጅነር በየነ በላቸው ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት የገለፁት።
የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ በወሰደው ልዩ እርምጃ በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃና የሌሎች መሰረተ ልማት ተደራሽነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ የውሃ ፕሮጀክቶች ለማጠናቅና በክልሉ መንግስት ልዩ በጀት ድጎማ የተለያዩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ለመገንባት በተወሰደው ልዩ እርምጃ የተለያዩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ጠቁመዋ
የተለያዩ የውሃ ፕሮጀክቶች መመረቅ የክልሉን የውሃ ሽፋንና የተጠቃሚዎችን ቁጥር እያሳደገ ይገኛል ብለዋል።ክልሉ ላለፉት 4 ዓመታት በሰራው ስራ ተጨማሪ 490 ሺህ ነዋሪዎችን የንፁህ መጠጥ ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ገልፀው የተደራሽነት ሽፋኑን ወደ 43% ማድረስ ተችሏል ብለዋል።
በክልሉ በቦንጋ፣ ሚዛንና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ከነዋሪዎች ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የውሃ እጥረት እንደምታየው የገለፁት ሀላፊው ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ጥናቶች ተጠናቆ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
በንፁህ መጠጥ ውሃና በሌሎች መሰረ ልማት ግንባታዎች የህብረተሰብ ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመምጣቱ ምስጋናቸውን አቅርበው አሁንም ለጋራ ተጠቃሚነት እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት እንደሚገባ ጠይቀዋል።
የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንደሚጠየቅ ያብራሩት ሀላፊው የተለያዩ አጋር አካላት ለንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክሮ እንድያስቀጥሉ ጠቁመዋል።
በንጉሴ ወልደየስ
