የህዳሴ ግድብ መመረቅ ተስፋ የሚናደርግባትን ኢትዮጵያ ፊት ለፊት እንዲናያት አድርጓል ሲሉ የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊ ወጣቶች ገለጹ

Spread the love

የታላቁ ኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ ክልላዊ ታላቅ የደስታ መግለጫና ድጋፋዊ ሰልፍ በቦንጋ ብዝሃ ዋና ከተማ ተደርጓል።

በሰልፉ ላይ የደስታ ስሜታቸውን በሚገልጹ ሀሳቦች፣ የተደራጀና በክልሉ ካሉት ስድስቱ ዞኖች ባህላዊ ክነት ባንዶች የታጀበ ሲሆን ከእነዝህ ሰልፈኞች ያነጋገርናቸው ወጣቶች ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊ ከተባበረ ምንም ጉዳይ እንደማይበግረው ያሳየንበት ምልክታችን ነው ብለዋል።

ከአስተያት ሰጪዎቹ አንዱ ወጣት አብራሐም ገይቲ የስራ መደብ፣ የኑሮ ደራጃ ሳይለይን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምፅ ያፀናው እና መጪውን ትውልድ ያዋኸደ አርማችን ብለው የዚህ ታሪክ ተቋዳሽ በመሆኔ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል ብለዋል።

ህዳሴ ግድብን አስመርቀን ብሩህ ተስፋ ይዘን አዲስ ዓመት የተቀበልንበት በመሆኑ ልዩ ስሜት ተሰምቶኛል ያለው ወጣት ታምራት ጋሙኖ: አባይ ለቤተሰቤ እና ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የህበረታችን ማሳያና የላብ ጠብታችን ምልክት መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ሀገር በጋራ አልመን ያለ ማንም እርዳታ ማሳካት የቻልንበት የህብረታችን ማሳያ ነው ያለችው ወጣት ጽዮን ኃይሌ ይህንን ማድረግ መቻላችን ቀጣይ ለሚንሰራቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች ትልቅ ብርታት እንደሆነም ገልጸዋለች።

ህዳሴ ግድብ ተመርቀው ሳይ የበለጠ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቶኛል ያለው ወጣት አበበ ፎርኩሉ ከጅምሩ ጀምሮ እስከ ፍፃሜ ድረስ በተለያዩ አማራጮች የተሳተፍንበት ልዩ ቅርሳችን በመሆኑ ደስታችንን እጥፍ ያደርገዋል ብለዋል።

ወጣት ደገፉ ዳወና እና ወጣት አስራት አዕሮ በበኩላቸቸው የአትችሉምን ፉከራ ከንቱ ያደረገና አድዋን በአሁኑ ትውልድ ያስታወሰው የድል ሰንደቅ ነው ብለው ወጣቱ ትውልድ በዚህ ተነሳሽነት በሁሉም አማራጮች ወደብ የማግኘት ወጥን ላይ እንዲያተኩር መንደርደሪያ በመሆኑ ሁላችንም በጋራ ወደሚናልማት ኢትዮጵያ ከፍታ ሊንተጋ ይገባል ነው ያሉት።

የሀገራችን ግማሽ ከመቶ በላይ የሚሆኑት ወጣቶች መሆናቸውን ያወሱት አስተያየት ሰጪዎች ይህን የፅናት ተምሳሌት የሆነውን ግድብ እንደ ወኔ ሰንቀን ለኢትዮጵያ ማንሰራራት በአንድ ድምፅ ልንሮጥ ይገባል ብለዋል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *