


አባይ የአርሶ አደር እናቶች መቀነት ተፈትቶ የተገነባ የላባችን ጠብታ እንደመሆኑ የሴቶችን ኑሮ ለማሻሻል የተዘረጋ መረብ ነው ብለው እንደሚያምኑ አስተያት ሰጪዎች ተናግረዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ወቅት ያነጋገርናቸው ወ/ሮ ብርሃኔ ብሩ ከመጀመሪያው ጀምሮ የራሴ እና የእናቶች የጋራ አሻራ ያረፈበት ግድብ በመመረቁ እጅግ ተደስቻለሁ ብለው ይህ ግድብ በሁሉም ኢትዮጵያዊ እናቶች ዘንድ የራስ ልጅ እስኪመስል በእናትነት ስሜት የተጋራንበት ተስፋችን ነው ያሉት።
የህዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ እያለም የተለያዩ የውስጥና ውጭ አሉባልታዎች መከበቡ ሳይበግረው ለምረቃ መብቃቱ እጅጉን እንዳስደሰታቸው የገለፁት ወ/ሮ አይናለም አድነው ለዝህም ቁርጠኛ አቋም የወሰደውን መንግስት እና መሪውን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አመስግነዋል።
ከዚህ በኃላ ብዙ አባዮችን ለመገንባት መነቃቃት እንደፈጠረላቸው የሚገልጹት አስተያየት ሰጪዎች በግንባታ ሂደት ውስጥ ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ ዜጎቻችን ሁሌም በልባችን ይኖራሉ ብለዋል።
አባይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ ቋንቋ ያግባባ መግባቢያችን ነው ያሉት ወ/ሮ ትክክል ዓለሙ እስካሁን ያደረግነውን ደጋፍ ዛሬ አካል ለብሰው በማየቴ ከእድለኞች አንዷ ያደርገኛል ብለዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀሳብ፣ በገንዘብ ፣ በጉልበት እና በተለያዩ አስተዋጽኦ ካበርን የማንወጣ ዳገት አይኖርም ያሉት አስተያየት ሰጪዎች እኛ ሴቶች ቤታችንና ሀገራችንን በማስተዳደርና ኃላፊነቶችን በመሸከም የሚንታወቅ እንደደመሆናችን ከዝህም በኃላ ወደ ኃላ የሚቀሩት ካሉ በማስተባበር የሀገራችንን ብልጽግና እውን እናደርጋለን ብለዋል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
