




ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተሟላ ሉዓላዊነት ለሀገራችን እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
ብሔራዊ ክብራችንን ሊያዋርድ በሚችል መንገድ እርዳታዎችን መቀበል እንደማይገባ አቶ የሺዋስ ተናግረዋል ።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ለማደናቀፍ ተገዳዳሪ ሀይሎች ጥቃቅን ችግሮችን በመምዘዝ የተለየ የትግል ስልት መፍጠራቸውን አቶ የሺዋስ አስረድተዋል ።
አባላት ንቁ ሆነው ማህበረሰቡንም በማንቃት እየተከሰቱ ያሉ ያልተለመዱ ፈተናዎችን ለመሻገር ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የአስተዳደር ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሳምሶን መለሰ የአፍራሽ ሀይሎችን የትግል ስልት በመለየት አባሉ ጠንክሮ ሊታገል ይገባዋል ብለዋል።
በልሳነ ብልጽና ንድፈ ሀሳብ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 6 ላይ አመራሩና አባላት ውይይት አድርገዋል ።
በቀረበው የመወያያ አጀንዳዎች ላይ ተሳታፊ አመራሮችና አባላት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የተረጂነት አስተሳሰቦችን አባላት በመታገል ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የአባላት ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።
ሀገር አፍራሽ አስተሳሰቦችን የሚያራምዱ ተገዳዳሪ ሀይሎች የሚያደርጉትን እኩይ ድርጊት ውስጠ አንድነትን በማጠናከር አባላት መታገል ይኖርብናል ብለዋል ተሳታፊዎች ።
የተረጂነት አስተሳሰብን ቁጭት በተሞላው መንገድ በመታገል ያሉንን ጸጋዎች ወደ ድል በመቀየር ለውጤታማነት መትጋት ይኖርብናልም ብለዋል።
ህዝብ አማራሪና ህገ ወጥ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን አስተማሪ ርምጃዎችን መንግስት ሊወስድ ይገባል ብለዋል።
አባሉ በየተቋማቸው የመንግስትንና የፓርቲ ስራዎችን ሚስጢራዊነት የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ያሉባቸው በመሆኑ ለአፍራሽ ኃይሎች ያልተገባ መረጃ ከማቃበል ሊቆጠቡና የድርጊቱን አስተሳሰብ አራማጆች ካሉም ሊከላከሉ እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል።
የተገዳዳሪ ሀይሎች አስተሳሰብን ሊመክት የሚችል የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ አባሉ በነቃ ተሳትፎ መሳተፍ ይኖርበታልም ተብሏል።
ያሉብንን መሠረታዊ ችግሮችን በመለየትና በመፍታት ውጤት ላይ ትኩረት ያደረገ የአሰራር ስልት በመከተል ለለውጥ መትጋት ይገባናል ብለዋል።
በልሳነ ብልጽግና የንድፈ ሀሳብ መጽሔት የቀረበው የመወያያ አጀንዳ ወቅታዊና ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ተሳታፊዎች በተገኘው ውጤት ከመኩራራት አስተሳሰብ በመውጣት ወደ ፊት ሊያሻግሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ መረባረብ ይገባልም ሲሉ ሰጥተዋል።
በቀረቡት አስተያየቶች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ከመድረኩ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል ።
በታጠቅ አበበ
