አቶ ታምሩ ቦኒ የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ

Spread the love

የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት፣ አቶ ታምሩ ቦኒን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ በሙሉ ድምፅ ሾሟል።

አቶ ታምሩ ከዚህ ሹመት በፊት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ሹመቱ የተከናወነው የዞኑ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ሲሆን፣ የቀድሞው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ጌታቸው ኬኒ በፓርቲና በመንግስት ሌላ ተልዕኮ መሆኑን ገልጸዋል።

የዋና አስተዳዳሪ ሹመት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ፣ የአመራር ለውጡ ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ለጉባኤው አስረድተዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም በቀረበው ሹመት ላይ ከተወያዩና የተለያዩ አስተያየቶችን ከሰጡ በኋላ፣ የአቶ ታምሩ ቦኒን ሹመት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *