ከ11ሺህ በላይ ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመረቀ።

Spread the love

በዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ፣ የከጪ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በገተገኙበት ተመርቋል።

በክልሉ መንግሥት የበጀት ድጋፍ የተገነባው የከጪ ከተማ ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ተመርቀው ለአግልግሎት ክፍት ሆኗል።

ፕሮጀክቱ በከጪ ከተማ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግርና የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት በዘላቂነት የሚፈታ እንደኾነም ታምኖበታል።

ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከክልሉ መንግስት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDG) በጀት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ ከ11ሺህ 700 በላይ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፣ በተለይም ትምህርት ቤቶችና ጤና ጣቢያን ንጹህ ውሃ እንዲያገኙ በማስቻል ረገድ የላቀ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዳለውም ተመላክቷል።

ፕሮጀክቱ ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች፣ የ300 ሜትር ኩዩብ በኮንክሪት የተሰራ የዉሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ እና የ19 ኪሎ ሜትር የቧንቧ መሰመር ዝርጋታ፣ የፓምፕ፣ ጀነሬተርና ትራንስፎርመር አቅርቦትና ገጠማ ስራዎችን ያካተተ ነወ።

በምረቃው መርሐግብር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴን ጨምሮ፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *