




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ SNV HORT LIFE 3 ፕሮግራም ጋር በመተባበር የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ተቋማዊ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ተወያይተዋል።
በመድረኩም በፕሮግራሙ እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን ማጠናከር እና ቀጣይ መሻሻል በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ፤በክልሉ በግብርናው ዘርፍ በተለያዩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ድጋፍ የሚከናወኑ ተግባራት የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ የሚኖረው ሚና የጎላ ነው ብለዋል።
በፕሮግራሙ ድጋፍ እስካሁን ሥራዎች ከተጀመሩ ወረዳዎች በጥንካሬ ከተመዘገቡት ሥራዎች ልምድ በመውሰድ ቀሪ አከባቢዎችም በፕሮግራሙ ታቅፈው አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆንና ግብርና ሥራ ውጤታማ እንዲሆን ከክልል ጀምሮ እስከታች ድረስ ሥራዎች በቅንጅት እንደሚሰሩም ተናግረዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
እስካሁን በአርሶ አደሮች በትንሽ ማሳዎች የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች እንደሆኑ በመጠቆም ቀጣይ ሥራዎች እንዲጠናከሩ በአርሶ አደር አመለካከት ማሻሻል እና አቅም ማጎልበት ላይ ሥራዎች በሰፊው ይከናወናሉም ብለዋል።
በሁሉም አከባቢዎች የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት እንዲቋቋም ያሳሰቡት አቶ ማስረሻ አዳዲስ ወደ ተግባሩ የሚገቡ አከባቢዎች አስቀድመው ሥራዎችን ከጀመሩ አከባቢዎች ልምድ እንዲቀመሩ ማድረግ እና በየአከባቢዎች የሚገኙ ሌሎች ፕሮጀክቶችም አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።
በአርሶ አደሮች ዘንድ ከተሻሻለው ምርጥ ዘር አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን የመፍታት ሥራዎች ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በክልሉ የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ተቋማዊ ለማድረግ ቀየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡም ያሳሰቡት አቶ ማስረሻ ቀጣይ በአርሶ አደሮች መስክ ትምህርት ቤቶች በሆርቲካልቸር ሰብሎች ብቻ ሳይሆን በሁሉም ግብርና ተግባራት ሥራዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ሥራዎች እንደሚሰሩም አመላክቷል።
ለሥራው ስኬታማነት በየጊዜው ሥራዎችን መቆጣጠር መከታተል እና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች ተጠናክሮ ይቀጥላሉም ብለዋል አቶ ማስረሻ በላቸው።
በፍቅር ከበደ
