የከንቲባ ችሎት የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ።

Spread the love

የአውራዳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ችሎት የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ ።

የለውጡ መንግስት የህዝብን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በከተማችን የከንቲባ ችሎት በ2017 ዓ/ም ስራ መጀመሩን የአውራዳ ከተማ ከንቲባ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ ተናግረዋል።

የከንቲባ ችሎት የከተማ መሬት አገልግሎት አሰጣጥ፣ የፍትህ እጦት፣የመልካም አስተዳደር ችግር፣የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚቀረቡ ጉዳዮች ላይ እየሰራ እንደሆነ አመላክተዋል።

በችሎቱ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ፣የሙስና ወንጀል፣የግብይትና ንግድ ጉዳይ፣የግብር እና መሰል ጉዳዮችን እንደማይታዩ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ ገልጸዋል።

ሁሉም የመንግስት ተቋማት ተገቢ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳይፈጠሩ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል ።

በከንቲባ ችሎት የተወሰኑ ውሳኔዎች በፍጥነት ምላሽ እንዲያገኙ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ከንቲባው አሳስበዋል ።

የአውራዳ ከተማ ነዋሪ አቶ ሻጋሮ ሻዎ በ2016 ዓ/ም ጀምሮ ችግራቸው እንዲፈታ ቅሬታ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳይሰጥ እየተንከባለለ ቆይቶ በከንቲባ ችሎት ምላሽ ማገኘቱን ይናገራሉ ።

በችሎቱ የቀረቡ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየተሰጠ ያለው ውሳኔ እንዳስደሰታቸው ተጠቃሚዎች ገልጸዋል ።

በከንቲባ ችሎት ቀደም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች በአስፈፃሚ ተቋማት ስደርስ የነበረውን መጉላላት የቀነሰ መሆኑን የከተማ ነዋሪ አቶ ገረመው መንገሻ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም በከንቲባ ችሎት ላይ በባለጉዳዮች በቀረቡት ጉዳዮች መሠረት የሚመለከታቸው አካላት በመሳተፍ የቀረቡ ጥያቄች ላይ ምላሽ እየተሰጠ እንደሆነም ተመላክቷል ሲል የዘገበዉ የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *