




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሴቶች ክንፍ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መርህ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክትና ማኒፌስቶ የማስተዋወቅ መርሀ-ግብር በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ፥ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ባስመዘገበችሁ ሁለንተናዊ ለውጥ የሴቶች ተሳትፎ ድርሻ የጎላ እንደነበረ ገልጸዋል።
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከሂደቱ እስከ ውጤት የተሳካ እንዲሆን እንዲሁም ‘መንታ ግቦችን’ እንዲያሳካ ሴቶች በአደረጃጀት በመኾን ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ሠላማዊ፣ ፍትሀዊ፣ ነጻና ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን ሁሉም ዜጋ ኃላፊነት እንዳለበት ያስገነዘቡት አቶ ግርማ፥ የብልፅግና ፓርቲ በእስካሁኑ ጉዞ በርካታ ድሎች ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
በተለዋጭ አለም-አቀፋዊ ሁኔታዎች እንዲሁም አዳጊ የልማት ፍላጎቶች ያልተመለሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት ፓርቲው በቁርጠኝነት ይሰራል ያሉት ኃላፊው፣
የመጡ ለውጦች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና በሂደቱም የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሴቶች ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ለምርጫው ስኬት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ ባስተላለፉት መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ አካታችን መገለጫ በመኾኑ በሚያከናውናቸው የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ተግባራት ሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው ብለዋል።
የሴቶችንና የወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የብልፅግና ፓርቲ በቁርጠኝነት እየሰራ መኾኑን የጠቆሙት ኃላፊዎ ይህ ተግባርም ቀጣይነት ኖር ውጤታማ እንዲኾን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መንታ ግቦች በማሳካት መፈጸም ይገባል ብለዋል።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመምረጥ፣ ለተጀመረው ልማትና ለተረጋገጠው ሰላም ዋስትና መስጠት እንደሚገባ ያሳሰቡት ወ/ሮ ሰብለፀጋ፥ ለምርጫ ስኬት ሴቶች በትጋት እንደሰሩ ጠይቀዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የሴቶች ክንፍ አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
