
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ ላይ እንደሚያካሄድ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌታቸው ኬኒ ገልፀዋል።
በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ፀጥታን ፣ የዝርፊያና የስርቆት ወንጀሎችን መከላከል እንዲሁም ከወሰን ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ የማድረግ ስራዎች ላይ ምክር ቤቱ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
ነገ በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ በ2018 ዓ.ም 6 ወራት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይቶች እንደሚደረጉ ዋና አፈጉባኤው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
በጉባኤው ላይ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የሁሉም ብሔረሰብ ተወካዮች እና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ምክር ቤቱ አስታውቋል ሲል ማሻ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
