ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

Spread the love

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ እና ለተጎጉ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በላኩት መልዕክት፣ በአደጋው ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።

በመሬት መንሸራተቱ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን የተመኙት ፕሬዚዳንት ፑቲን፣ አደጋው ያስከተለውን ጉዳት ተከትሎም የሩሲያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጎን መቆሙን አመላክተዋል።

በመሬት መንሸራተቱ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን የተመኙት ፕሬዚዳንት ፑቲን፣ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችም በፍጥነት እንዲያገግሙ ያላቸውን መልካም ምኞት አስተላልፈዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *