




በአመያ ከተማ አስተዳደር፣ ጨታ ቀጭቀጫ ቀበሌ በ11 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የበጋ መስኖ ስንዴ አጨዳ በይፋ ተጀምሯል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጄኔ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
“አይሞከርም” የሚለው እሳቤ በፅኑ አቋም ወደ “ይቻላል” ተቀይሮ ውጤት መገኘቱ ተገልጿል።
የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ ተስፋ የተጣለበትና የብልጽግና ፓርቲ ስኬት መገለጫ መሆኑ ተጠቅሷል።
ስራው ከኢኮኖሚ ጥቅሙ ባለፈ የአርሶ አደሩንና የመንግስትን የአብሮነት ግንኙነት ያጠናከረ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
አርሶ አደሮች ካለፈው ዓመት ልምድ በመነሳት በቀጣይም በስፋት ለማምረት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።
