



በጉብኝታቸውም በሸካ ዞን የኪ ወረዳ በጪ ቀበሌ በአርሶ አደሮች በክላስተር የለማ የሩዝ ምርት አሰባሰብ ሂዴትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በተደራጁ ወጣቶች በፊደና አዲስ ብርሃን ቀበሌ እየለማ የሚገኙ የቅመማ ቅመም ( ቁንዶ በርበሬ፣እርድ) ማሳም የጉብኝቱ አካል ነበሩ።
ጥምር እርሻ(ሙዝ ፣ፓፓያ፣አናናስና ቡና)፣የማር መንደርን የጎበኙ ሲሆን በኩብጦ ቀበሌ የአቶ ደረጀ ዳልቶ የቡና እንዱስትሪ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።
ዶክተር ለገሰ ቱሉ በጉብኝቱ ወቅት አካካባቢው በምግብ ራስን ለመቻልም ሆነ በርካታ ምርት ለመሰብሰብ ምቹ በመሆኑ በስፋት በማምረት ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
አርሶ አደሮች ምርት ማምረት ብቻም ሳይሆን ምርታቸውን በማስፋትና የገቢ አቅማቸውን በማሳደግ ኑሯቸውን ማሻሻል እንደሚገባ የተናገሩት ዶክተር ለገሰ ቱሉ የገጠር ኮሪደር ልማትን ማጠናከር እንደሚገባም አክለው ገልፀዋል።
ዶክተር ለገሰ ቱሉ እና ልዑካቸው በምኖራቸው ቆይታ በዞኑ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል።
በጉብኝቱ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞን ጨምሮ የሸካ ዞን፣የየኪ ወረዳና ቴፒ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
