ምርጫ ቦርድ 30 በመቶ የሚሆነውን የመንግስት የመጀመሪያ ድጋፍ ለፓርቲዎች ለቀቀ

Spread the love

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 30 በመቶ የሚሆነውን የመንግስት የመጀመሪያ ድጋፍ ለፓርቲዎች ለቅቄያለሁ አለ።

ቦርዱ ለተመዘገቡ እጩዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የእጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል።

የቦርዱ የህግ አማካሪ አይተነው ደበበ የእጩዎችና የፓርቲዎችን ስም፣ ምልክት እና ምስል በድምፅ የሚወሰንበት ሥርዓት መደንገግ የምርጫ ሂደቱ ግልፅ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሆነ ተናግረዋል።

የድምፅ መስጫ ወረቀት የእጩዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስም መለያ ምልክትና የእጩዎችን ምስል በመያዝ ታትሞ የተዘጋጀና መራጮች ለሚፈልጉት እጩ ድምፅ የሚሰጡበት ወረቀት መሆኑንም ገልጸዋል።

በመድረኩ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉን ጨምሮ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን÷ ምርጫ ቦርድ እስካሁን የሰራቸውን ስራዎች አቅርቧል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *