




በሮው ከወርልድ ቪጅን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተጎዱ መሬቶችን መልሶ ማልማት ላይ ያተኮረ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብትና የአነስተኛ መስኖ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ አሚኖ ሙሃመድ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደገለፁት በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ መሬት በከፍተኛ መጠን እየተጎዳ መምጣቱን ገልፀዋል።
የተጎዱ መሬቶችን መልሶ በማልማት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በመንግስትና በአጋር አካላት ድጋፍ በርካታ ተግባራትን እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው ይህ በወርድ ቪጅን ድጋፍ የሚሰጠው ስልጠና የዚሁ ተግባር አንዱ አካል መሆኑን ገልፀዋል።
ስልጠናው የተጎዱ መሬቶችን በዘላቂነት ለማልማት ለይቶ ወደ አንድ ቋት ማስገባትን አላማ ያደረገ የSolite ሶፍትዌር ስልጠና እንደሆነም አሳውቀዋል ።
ወርድ ቪጅን ኢትዮጵያ በክልል ካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ የማህበረሰቡን ህይወት የቀየሩ ድጋፎችን ስያበረክት መቆየቱን ገልፀው አገልግሎቱን ለማስፋፋት በክልሉ ቢሮውን ከፍቶ በሁሉም ዞኖች ተደራሽ ለመሆን ወደተግባር መግባቱን ገልፀዋል።
የወርድ ቪጅን ኢትዮጵያ (FMNR) movement catalyist ፕሮጀክት የክልሉ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ቶማስ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በዋናነት የተጎዱ መሬቶችን መልሶ ማልማት የሚያስችል ፕሮጀክትና የማህበረሰብ ድጋፍ ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ ገልፀው በገዋታ አከባቢ ቀድሞ ለተደራጁ ማህበራት 100 የቦንጋ በግ፤ 90 ግደርና 10 ኮርማና ከ1500 በላይ ዶሮ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል።
ፕሮጀክቱ በክልሉ ቢሮውን መክፈቱ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋፋት እንዳስቻለው ጠቁመው ፕሮጀክቱ በክልሉ ከድስቱም ዞኖች ለተመረጡ ወረዳዎች ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ጠቁመዋል።
ስልጠናው ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚካሄድ የተገለፀ ስሆን በፕሮጀክቱ የተሰሩ መልካም ልምዶችም እንደሚጎበኙ ከመርሃ ግብሩ ለማወቅ ተችሎዋል።
በንጉሴ ወልደየስ
