




”የጉባ ብስራቶች፣የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ክልል ዓቀፍ ህዝባዊ የዉይይት መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ አውራዳ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በህዝባዊ የዉይይት መድረኩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ እና የካፋ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ታከለ ታምሩ ተገኝተዋል።
ከክልልና ከዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪም የአውራዳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ እንዲሁም ከተለያዩ ማኅበራዊ መሠረቶች የተወጣጡ የተለያዩ ሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛል።
ህዝባዊ የውይይት መድረኩ ሕዝቡን ያሳተፈ የመደመር መንግስት ትሩፋት የሆኑ ስኬቶችና ቀጣይ ብሥራቶች ዙሪያ በጋራ በመወያየት ድሎቹ ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማስችል ነው።
ከተለያዩ ማኅበራዊ መሠረቶች ከተወጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሚደረገው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ በልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር የሚደረግ ሲሆን ለሚነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል።
