የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል በደካ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

Spread the love

በካፋ ዞን ደካ ከተማ “የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።

የህዝብ የውይይት መድረክ መፈጠሩ በህብር የተጀመረውን ልማት በህብር ለመጨረስ የሚረዳ እንደሆነ በዚሁ ወቅት ተመላክቷል።

በመድረኩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ለማ መሰለ፣የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጥናፉ ኃይሌ፣ የደካ ከተማ ከንቲባ አቶ አድነው ኃይሌ፣ የደካ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ሻጊ ጨምሮ የካፋ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አስተባባሪዎችና የስራ ኃላፊዎች ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ በደካ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች እና ከማህበራዊ መሠረት የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የዘገባው የደካ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *