
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ በክልሉ ለሚገኙ ዐቃቢያነ ህግ በአዲሱ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቤተልሔም ዳንኤል የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻልና ለማዘመን በየወቅቱ የሚወጡ ማሻሻያዎችን በተገቢው አቅም መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።
ስልጠናው በዋናነት በአዲሱ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017፤ በወንጀል ስነስርዓት ማሻሻያና የዓቃቤ ህግ ስነስርዓት ደንብ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ገልፀዋል።
ከፍትህ አስተዳደር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ የፍትህ ተቋማት ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸው ገልፀው ዓቃቤ ህጎች ከምርመራ እስከ ውሳኔ ያሉ ህደቶችንና አፈፃፀሙን መከታተል እንደሚገባቸው ገልፀው ለዚህም ከየትኛውም የስነምግባር ጥሰት የራቁ ልሆኑ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል ።
በህዝብና በሀገር ጥቅም ላይ ጉዳት ልያደርሱ የሚችሉ ወንጀሎችን ለመቅረፍ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠይቀው ቢሮው የዓቃቤ ህጎችን ግንዛቤ ለማሳደግ ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውል ገብቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ስልጠናው ከካፋ ዞን ከሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ ዓቀቤ ህጎች የተሳተፊ ስሆን በተመሳሳይ በክልሉ ባሉት ስድስቱም ዞኖች ለሚገኙ ዓቃቤ ህጎች እየተሰጠ እንደሆነም ገልፀዋል።
የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 ላይ ያቶከረው ስልጠና በቢሮው ታክስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች ዳይረክቶረት ዳይረክተር በአቶ ውብሸት ጀምበር እየተሰጠ ይገኛል።
በንጉሴ ወልደየስ
