ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ይካሄዳል፡፡

በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከም/ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የስብሰባው ሙሉ ሂደት በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ መሆኑንም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፋና ዲጂታል ገልጿል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *