




የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቧል።
ባለፉት ስድስት ወራት ፓርቲው የህዝቡን ተጠቃሚነትና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት በጽ/ቤቱ ስትራቴጂክ ስራ አመራርና ኢኮቴ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ አንተነህ አየለ ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።
በብልጽግና አሻጋሪ እሳቤዎች በመመራት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ለብልጽግና ጉዞ ስኬት መሠረት የሚጥል ተግባራት መከናወኑን በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ውጤታማ የህዝብ ንቅናቄ የተመሩበት አቅጣጫ የፓርቲው ኢኒሼቲቮች በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ በመተግበር የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎችን ማሳለጥ መቻሉ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
የትርክት የበላይነትን መያዝ የሚያስችል ተከታታይ የመልዕክት ቀረጻዎችን በመስራት ለወንድማማችነትና እህትማማችነት አስተሳሰብ መጎልበት ተጨባጭ አስተዋፆ የሚያበረክቱ ተግባራት መከናወኑም ኃላፊዉ ገልጸዋል።
