በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ በተከሰተው የአባ ሳንጋ በሽታ ህብረተሰቡ ላልተወሰነ ጊዜ በዞኑ ውስጥ ጥሬ ስጋ መመገብ እንደማይገባቸው የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ

Spread the love

በምዕራብ ኦሞ ዞን በሱሪ ወረዳ በኮካ ቀበሌ የተከሰተው የአባ ሳንጋ በሽታ የመከላከል ሥራዎች ላይ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የዞኑ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሼማጂ ጉሪጭማ እንደተናገሩት በዞኑ በሱሪ ወረዳ በአባ ሳንጋ በሽታ የሞተ ሰው አለመኖሩን ያስታወቁት ኃላፊው በዞኑ አርብቶ አደር መምሪያ ኃላፊ አማካይነት ሰባት ሰዎች በአባ ሰንጋ በሽታ ሞቱ ተብሎ ለDW የተሰጠዉ መረጃ ስህተት፣ ያልተገመገመና በዞኑ ጤና መምሪያ በኩል የማይታወቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በወረዳ በተከሰተው የአንትራክስ በሽታ በበሽታው የተጠቃው ከብቶች የተመገቡ እና ንኪኪ የነበራቸው 69 ሰዎች ታሞ ህክምና ማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል።

አያይዘውም ከ3ሺህ በላይ ህዝብ ልያክም የሚችል የተለያዩ መድኃኒት እና ቁሳቁሶች ተደራሽ መደረጉ አስገንዝበዋል።

በሽታው ተላላፊ በመሆኑ በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና በአጎራባች ዞን ወረዳዎች ጥሬ ስጋ እንዳይመገቡ አስጠንቅቀዋል።

የዞኑ ግብርና እና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ሃላፊ አቶ መልኬ ኬላኬ በበኩላቸው በዞኑ ከ70ሺህ በላይ እንስሳት ልያክም የሚችል ክትባት መኖሩን ጠቅሶ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በሽታው ለመከላከል ከ9ሺህ በላይ እንስሳት ልከትብ የሚችል መድኃኒት እንዲሁም በበሽታው የታመሙ እንስሳት ልያክም የምችል ከ1,350 በላይ መድኃኒት ስርጭት ማድረጋቸው አቶ መልኬ አክለዋል።

በሱሪ ወረዳ ከ3ሺህ 625 በላይ ከብቶች እና 150 ፍየሎች ክትባት መስጠት መቻላቸውን ተናግረዋል።

በዞኑ በሽታው ለመከላከል ግብረሀይል ተቋቁመዉ ከፍተኛ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *