“ማርች 8” ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ በኮንታ ዞን በሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት የተሰሩ ስራዎችን ኤግዚብሽን ተካሄደ።

Spread the love

ኤግዚቢሽኑን የበፌደራል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ሁሪያ አሊ እና የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ከፍተዋል።

በፌደራል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሁሪያ አሊ የተመሩ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ሴት አመራሮች ልዑካን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ በኮንታ ዞን በሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት የተሰሩ ስራዎችን መጎብኘት ጀምረዋል።

በኤግዚቢሽኑ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ በክልሉ ብሎም በዞኑ ሴቶች በተለያዩ ኢኮኖሚያቸውን የሚያሳድጉ ሰፊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ኤግዚቢሽኑን ያስጎበኙት የኮንታ ዞን ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ድንቅነሽ በፍቃዱ በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሴቶች በሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት ተደራጅተው ውጤታማ እየሆኑ መሆናቸውን በመግለፅ ለኤግዝቪሽኑ የቀረቡ ተግባራት በዞኑ አመያ ከተማ አስተዳደር፣ በኤላ ሀንቻኖና በአመያ ዙሪያ ወረዳ የተሰሩ ተግባራት መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል ማርች 8″ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል በኮንታ ዞን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል ሲል የዘገበዉ የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *