በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

Spread the love

በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የጎረቤት ሀገራት እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሀሳብ ከትላንት ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል።

በጉባኤ ላይ ለመታደም ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት የመጡ እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በጉባኤው መክፈቻ ላይ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

በዛሬው እለትም ከፍተኛ አመራሮች የእንጦጦ ፓርክን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በፓርኩ አስጎብኝዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *