ሎጁ ለክልሉ ተጨማሪ ውበትና የኢኮኖሚ ምንጭ ነው- ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

Spread the love

የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጂ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሌሎች የፌዴራል የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ተመርቋል።

በኮይሻ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ስር የለማው የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጂ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተጨማሪ ውበት ያጎናፀፈ እና ተጨማሪ የኢኮኖሚ ምንጭ የሚሆን ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገልፀዋል።

ክልሉ ተፈጥሮና ሰው ከልብ ተዋዶ የሚኖርበት ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ብልጽግና መራሹ መንግስት የነበረውን ጥብቆ ለነገው ትውልድ ትልቅ አሻራ እያሳረፈ መሆኑን ጠቁመዋል።

መንግስት በየአካባቢው ያሉ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን ወደ የሚጨበጥ ልማት አየቀየረ የዜጎችን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያደረገው ጥረት ተጨባጭ ማሳያ እንደሆነም ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ገልጸዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *