


የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ኡመድ ኡጁሉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ኡመድ ኡጁሉና ልዑካቸው በክልሉ ካፋ ዞን ውሽውሽ ሻይ ተክል ልማት አካባቢ ሲደርሱ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ተቀብለዋቸዋል ።
ከርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ጋር ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አብረው ተገኝተዋል ።
ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጁሉና ልዑካቸው በኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የውሽውሽ ሻይ ልማት የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በክልሉ የአስተዳደርናፖለቲካ መቀመጫ በሆነችሁ ቦንጋ ከተማ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት እና የጋምቤላ ክልል መንግስት የጋራ የሰላምና ልማት ምስረታ በነገው ዕለት ይደረጋል።
በታጠቅ አበበ
