በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች እየተከናወነ ያለው የበጎ ተግባራት ዜጎችን በተጨባጭ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል:-ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሁሉም አከባቢዎች እየተከናወነ ያለው የበጎ ተግባራት ዜጎችን በተጨባጭ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገልጸዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተደድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በክልሉ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በክልሉ ስላደረገው የአቅመ ደካሞች ቤት መስሪያ እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፊ በክልሉ ህዝብና መንግስት ስም አመሰግነዋል።

የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ መንግስት አካታች ማህበራዊ ልማት ለማረጋገጥ እያደረገ ያለው ዘርፈ ብዙ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሀገር ደረጃ በጣም ሰፋፍ የሆኑ የልማት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሆነ የገለፁ ሚኒስትሯ በመተባበርና በአንድነት የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚቻልም አብራርተዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከGGGI ከተሰኘ አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ለቤቶቹ ግንባታና ለቤት ቁሳቁስ ግዥ ከ12.5 ሚልዮን ብር በላይ በጀት እንደተመደበም ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገልጸዋል።

ለአቅሜ ደካሞች የሚገነባዉ ቤትም የተለያዩ ክፍል ያሉት መኖሪያ ቤት ፣መፀዳጃ ክፍል ፣ የሶላር ኃይል አገልግሎት፣ የቆሻሻ ማስወገጃ ሥርዓት እና የውሃ ማጠራቀሚያ አማራጭ ያለው መሆኑን ዶ/ር ኤርጎጌ አስረድተዋል ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለ150 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል።

በክልሉ በክረምት ወራት የበጎ ተግባር 540 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች ሰርቶ ለማስረከብ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራ እንደሆነም ተብራርቷል።

የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው በዞኑ በለውጥ መንግስት መሪነት እየተከናወነ የሚገኝ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት የሚያሰመሰግን እንደሆነ ጠቁመዋል።

በመርሃግብሩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ የችግኝ ተከላ መርሃግብርም ተካሂደዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *