fvfdvg

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ እና የኢፌዲሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አቅሜ ደካሞች የቤት ግንባታዉን ዛሬ በይፋ በዳዉሮ ዞን በታርጫ ከተማ አስጀምረዋል።

የኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከGGGI ከተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያስገነባው አምስት ደረጃቸውን የጠበቁ የመኖሪያ ቤቶች ሲጠናቀቁ በውስጣቸው ሙሉ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች እንደሚሟሉ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም በዞኑ አቅም ተገንብተዉ ለአረጋዊያንና ለአቅመ ደካሞች የተላለፈው የመኖሪያ መንደር ጉብኝት የተደረገ ሲሆን መሰል ሥራዎችን ለማጠናከር ሁሉም የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል።

ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች የሚገነባላቸው ዜጎች በሰጡት አስተያየት የዕድሉ ተጠቃሚዎች መሆን መቻላቸው በእጅጉ አስደስቶናል ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዎ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የዳዉሮ ዞንና እና የታርጫ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *