




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ለሶስተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸው የመካከለኛ እና ከፍተኛ ማዕረግ ሽግግር ሰልጣኝ የፖሊስ መኮንኖችን እያስመረቀ ይገኛል።
ሰልጠኞቹ የቆይታ ጊዜያቸዉን የሸፈኑ ከዋና ሳጅን ወደ ረዳት ኢንስፔክተር እና ከኢንስፔክተር ወደ ዋና ኢንስፔክተር ሽግግር የሚያደርጉ ሲሆኑ የፖሊስ አመራርነት አቅም ግንባታ ስልጠና የወሰዱ ናቸዉ።
በምረቃ መረሐ ግብሩ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሮች፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።
በፍቅር ከበደ
