



በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እስታንዳርዱን አሟልተው ወደ ትግበራ መግባቱን መመልከት ተችለዋል።
የለውጡ መንግስት በትምህርት ሴክተር ላይ ይዘው ከመጣባቸው ኢኒሼቲቮች ቀዳሚው ቅድመ አንደኛ ትምህርት ነው ያሉት የአዲስ ፋና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አበበ ቢቂላ: የትምህርት ጥራት ችግርን ከስሩ ለማከም አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
የቅድመ መደበኛ ትምህርት በእስታንዳርዱ መሠረት ለመተግበር የተርጫ ከተማ አስተዳደር ከ 7.3 ሚልየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለህፃናት ምቹ ከባቢ መፍጠር የሚችል መመገቢያ አዳራሽን ያካተተ ግንባታ በ 3 ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል።
በ2018 በጀት ዓመት 215 ተማሪዎችን ተቀብለው እያስተማሩ እንዳለ የገለጹት መ/ር አበበ ወደ ምገባ ፕሮግራም ለመግባት ህብረተሰቡን ያሰተፈ ውይይትና ዝግጅት እንዳጠናቀቁ አክለው ገልጸዋል።
ለምገባ ፕሮግራም ህብረተሰቡ፣ ትምህርት ቤቱና የከተማ አስተዳደሩ በገራ በመሆን አስተዋጽኦ እያደረጉ ሲሆን የደሃ ደሃ ተማሪዎችን በነፃ መመገብ በሚያስችል መልኩ ዝግጅት መደረጉንም አስታውሰዋል።
ፕሮግራሙ ራሱን ችሎ እንዲመራና በተለዩ መምህራን ትምህርት እየሰጠ በመሆኑን የጠቆሙት መ/ር ጌታቸው ሀብቴ: መንግስት እየወሰደ ባለው ሪፎርም መርህ የትምህርት ጥራትን ከመሠረቱ እያጠናከሩ ለመምጣት አወንታዊ ተፅኖ እንደሚያሳድርም ተናግረዋል።
ቅድመ አንደኛ ላይ በተጠናከረ መንገድ ከተሰራ ለመካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ተማሪዎችን ከማዘጋጀት ባሻገር እንደ ሀገር በኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ተጽዕኖ የሚፈጥረውን ልዩነት በማጥበብ ፍትሐዊ የትምህርት ተደራሽነትን እውን እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
