በክዋኔና በአካባቢ ኦዲት ግኝት አመላለስ ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት በቅንጅትና ቁርጠኝነት መወጣት አለባቸው ፦ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ከክልሉ ምክር ቤት ኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ-ኃይል ጋር በክዋኔና በአካባቢ ኦዲት ግኝት አመላለስ ዙሪያ የምክክር መድረክ በቦንጋ አካሂደዋል።

ለመድረኩ ላይ በክዋኔና በአካባቢ ኦዲት ግኝት የእርምት እርምጃ አወሳሰድ ያለበት ደረጃ ለመከታተል የተዘጋጀ ቼክ ሊስት

ዋና ኦድተር ጀኔራል አቶ አስራት አበበ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ዓላማውም በኪዋኔና በአካባቢ ኦዲት ግኝት አመላለስ በተሰጠው ግብረ መልስ ርምጃ ስለመወሰዱን ማረጋገጥና ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር ነው።

መድረኩን የመሩት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤና የግብረ-ኃይሉ ሰብሳቢ አቶ ወንድሙ ኩርታ በግብረ ኃይሉ በተሰራው ስራ በክልሉ በፋይናንሻል ኦዲት ላይ አመርቂ ውጤት ማስመዝቡን በማንሳት በኪዋኔ ኦዲት የሚታዩ የአፈጻጸም ውስንነቶችን ማረምን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ግብረ-ኃይሉ የኪዋኔ ኦዲት ግኝትን ከመገምገምና አቅጣጫ ከማስቀመጥም በላይ ወርዶ በቦታው ድጋፍና ክትትል በማድረግ ክፍተቶችን መለየቱ ውጤቱን ለማሻሻል ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።

ለውጤታማነቱም በየደረጃው ያሉ አካላት ርብርብና ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ በማንሳት ደርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የክልሉ ዋና ኦድተር ጀኔራል አቶ አስራት አበበ ምልከታ የሚደረግባቸው ተቋማትና ድርጅቶች በተቀመጠው የአሠራር ስርዓት በመመራት ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጥ ለህዝብ ተጠቃሚነት ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

ግቡም በአፈጻጸም ዝቅተኛ በሆኑ መስሪያ ቤቶች ላይ አስተማሪ የሆኑ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ መሆኑን በመግለጽ የባለድርሻ አካላትና የሚዲያ አካላት ሚናው በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የውይይቱ ላይ ተሳታፊዎች በገጠርም ሆነ በከተማ የሚሰሩ የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪዎች በተቀመጠው አግባብ ከማልማት፣ የህብረተሰብን ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥና የአካባቢውን ተፈጥሮና የዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅ ሚዛናዊነት ለማስጠበቅ ክትትልና ድጋፊ ወሳኝ በመሆኑ በቁርጠኝነት መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የድጋፍና ክትትል ተግባራት በካፋ ዞን፣ በቤንች ሸኮ ዞን እና በሸካ ዞን የሚገኙ የገጠር ኢንቨስትመንት፣ ኢንዱስትሪዎች፣ የሆተል ኢንቨስትመንት እና ኢንተርፕራይዞች ላይ ክትትል እንደሚደረግ ተገልጿል።

በምክክር መድረኩ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም፣ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ፣ ዋና ኦድተር ጀኔራል አቶ አስራት አበበን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እና ሌሎች የግብረ ኃይሉ አባላት ተገኝቷል።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *