




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶች የየ2016 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ መክፈቻ ፕሮግራም በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በመክፈቻው ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በክልሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን በጎ ፈቃደኞች በማሳተፍ በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን መርዳት መቻሉን ተናግረዋል ።
በጎነት ትልቁ የሰብዓዊነት መገለጫ፣መሰጠትን የሚፈልግ ሰናይ ተግባር ነው። በሁሉም አካባቢዎች ህዝባዊ ቅርጽ እንዲይዝ በትኩረት መስራት ይገባናል ብለዋለ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን ባህል በማድረግ ከባለፈው ዓመት በላቀ ሁኔታ መስራት ይገባልም ብለዋል።
በትምህርት ስራዎች ፣ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር ፣በከተማ ውበትና ጽዳት ስራዎች እንዲሁም ለወባ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በማጽዳት ወጣቶችንና ህብረተሰቡን በማስተባበር በትኩረት ሊሰራም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል ።
የክልሉ ሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቡድን ስሜትን በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል ።
በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የስምሪት መርሐ-ግብር በ13 የስምሪት መስኮች 559 ሺህ 593 ወጣቶች እንደሚሳተፉ 559 ሺህ 503 ተናግረዋል ።
በዚህም 1 ሚሊዮን 956 ሺህ 267 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ 590 ሚሊዮን 643 ሺህ 021 ብር የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን ለማከናወን መታቀዱን ጠቅሰዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንቅስቃሴ ማህበራዊ ትስስርን፣ አንድነትንና ፍቅርን የበለጠ እንዲጠናከር ማድረግ ያስቻለ ነው፡፡
ይህ ተግባር መንግሥትን ከከፍተኛ የገንዘብ ወጭ በማዳን የአገራን ኢኮኖሚ ማጎልበት ውስጥ ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡
ባለፈው የክረምት ወራት በጎ አድራጎት ንቅናቄ ከ125 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ 470 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ በማድረግ ከመንግስት ካዝና ሊወጣ የነበረውን ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ችለናል ብለዋል።
የክልሉ ሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ራሔል ለዊ በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ
በዘንድሮው የክረምት መርሃግብር በ13 የተለያዩ መስኮች ወጣቶችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በማሰመራማራት የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወኑም ወ/ሮ ራሔል በዕቅድ አቅርበዋል።
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች በየብዝሀ 34 ቤቶች በክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች በአዲስ እንደሚገነቡም ዕቅድ መያዙን ወ/ሮ ራሔል ለዊ አብራርተዋል ፡፡
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመክፈቻ ፕሮግራም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጸጋዬ ማሞ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ከየዞኑ የተጠሩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በታጠቅ አበበ
